የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎትድርጅት ከኢ.ኤም.ኤስ ደንበኞች ጋር ታህሣስ25 ቀን 2005 ዓ.ም የግማሽ ቀን ውይይትበኢንተርኮንትኔታል ሆቴል አካሄደ፡፡ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግደይ ገ/ዮሃንስ እንደተናገሩት ኢ.ኤም.ኤስ በሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች የደንበኞችን አስተያየትመሠረት በማድረግ ጠንካራ ጐናችንንለማስፋት እና በታዩ ክፍተቶች ላይ ማስተካከያበማድረግ በቀጣይ
የተሻለ ደንበኛ ተኮርአገልግሎት ለመስጠት መሆኑን አብራርተዋል፡፡በዕለቱም የሥራ ሂደቱ ሥራአስኪያጅ ወ/ሪት ይፍቱሥራ መኮንንኢ.ኤም.ኤስ ከተቋቋመበት1981 ዓ.ም ጀምሮ ያሣለፋቸውን የለውጥ ምዕራፎችየሚያስታውስ የመነሻ ፅሁፍያቀረቡ ሲሆን በሂደትያጋጠማቸውን ችግሮች እናየተወሰዱ መፍትሄ አቅጣጫዎችንም በመጥቀስለውይይት አቅርበዋል፡፡በውይይቱም ደንበኞች በርካታ ገንቢ ሃሣቦችን ያነሱ ሲሆን በተለይ በደንበኞች አያያዝ ላይበፈጣን መልዕክት፣የቤት ለቤት ቅበላና ዕደላ አገልግሎት ላይ፣በመልዕክት መቀበያ ስልኮች እናየቅሬታ አሰማም ላይ፣በቢሮ አደረጃጀት እና በዓለም አቀፍ መልዕክት ቅብብሎሾች ዙሪያጠንካራ እና ደካማ ጐኖች አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅምሁሉንም አስተያየቶች በሙሉ ልብ የተቀበሉሲሆን ኢ.ኤም.ኤስ ባገኘው ዓለም ዓቀፍ እውቅና የደንበኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑንአውስተው መታረም የሚገባቸውን በማስተካከል በቀጣይ የተሻለ አገልግሎትይዘው ለመቅረብ ቃል የገቡ ሲሆን ደንበኞች ለሰጧቸው ገንቢ አስተያየቶችም አመስግነዋል፡፡በመጨረሻም አንዳንድ ያነጋገርናቸው ደንበኞች እንደተናገሩት ድርጅቱ የደንበኞችን ንጉስነትበተግባር ያረጋገጡ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆንበተጨማሪም ድርጅቱበተለያዩ ጊዜያት በደንበኞችዘንድ የሚፈጠረውን ቅሬታ ሆነ እርካታ በማዳመጥ ለመወያየት የሚከተለው አሰራር የሚያስመሰግንመሆኑን ጠቁመዋል፡፡